Monday, October 7, 2024
spot_img

የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የመስቀል በዐል ንግግር በመንግሥት ጫና ይዘቱ መቆረጡ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 20፣ 2014 ― የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በመስቀል በዐል ያቀረቡት ንግግር በመንግስት ጫና መቆረጡ ተነግሯል፡፡

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በመስቀል በዐል ላይ ያቀርቡታል የተባለው ንግግር ቀድሞ ለዚሁ በዐል በተዘጋጀ መጽሔት ላይ የታተመ ሲሆን፣ በዚሁ በታተተመው ንግግር ሙሉ ይዘት ላይ አቡነ ማትያስ ‹‹እባካችሁ የመስቀሉን ሰላምና እርቅ እናክበር›› የሚል መልእክት በማንሳት ስለ ሰላም እና እርቅ አስፈላጊነት አብራርተዋል፡፡

በዚሁ ማብራሪያ ወቅት በድርድርና በውይይት፣ በሰጥቶ መቀበልና በይቅርታ የማይፈታ ችግር የለም ያሉት ብጹእ አቡነ ማትያስ፣ እነዚህን እንዳናደርግ ማን ከለከለን ሲሉም ጥያቄ ሰንዝረዋል፡፡ አያይዘውም ከእነዚህ በቀር የሚጠቅመን ምን አለ በማለትም፣ የተሻለ ነው ያሉት ይህ አማራጭ እያለ ለምን የሰው ሕይወት ይጠፋል፣ ለምን ንብረት ይወድማል፣ ወንድምስ በወንድሙ ላይ ለምን ይጨክናል፣ አሁንስ ሄዶ ሄዶ ወደ ውይይት መግባት መቼ ይቀራል፣ ነገር ግን እዚህ ሳይደረስ ቢደረግ መልካም ነበር ብለዋል፡፡

ይኸው በመስቀል በዓል ቀን ሳይነበብ ቀርቷል የተባለው ንግግር፣ ተቆርጦ እንዲቀር የተደረገው በአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች ጫና መሆኑን ለሕወሓት ቅርበት ያላቸው ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img