Friday, November 22, 2024
spot_img

በካርቱም ከታጣቂዎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 5 የሱዳን የደኅንነት አባላት ተገደሉ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 19፣ 2014 ― በካርቱም ከታጣቂዎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 5 የሱዳን የደህንነት አባላት ተገድለዋል።

የደህንነት አባላቱ የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት ሳይሆኑ እንዳልቀሩ ከተጠረጠሩ ታጣቂዎች ጋር በከፈቱት ተኩስ ነው መገደላቸው የተነገረው።

የሱዳን የብሔራዊ የደህንነት አገልግሎት ባወጣው መግለጫ አምስት አባላቱ በተሰነዘረባቸው ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን እንዳስታወቀ ኤፒ ዘግቧል።

አባላቱ የተገደሉት የአይ ኤስ የሽበር ቡድን አባላት ናቸው በሚል የተጠረጠሩ ሰዎችን ለመያዝ ስምሪት ላይ እያሉ በተከፈተ የተኩስ ልውውጥ እንደሆነም ተገልጿል።

በዚህ አደጋ ተሳትፈዋል በሚልም 11 የውጭ አገራት ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የአገሪቱ የደህንነት ተቋም ገልጿል።

አይኤስ የተሰኘው የሽብር ቡድን እስካሁን በሱዳን ለተሰነዘረው ጥቃት ሃላፊነት መውሰዱን ያልገለጸ ሲሆን፣ የሱዳን መንግስት ግን ጥቃቱ በዚህ የሽብር ቡድን ደርሷል ብሏል።

አሜሪካ ከዚህ በፊት አይኤስ የሽብር ቡድን በሱዳን ሊንቀሳቀስ እና ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል የሚል ስጋት እንዳላት ገልጻ ነበር።

የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ በደህንነት አባላቱ ሞት ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img