Saturday, October 5, 2024
spot_img

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ነገ ለሚያደርጉት ሕዝበ ውሳኔ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 19፣ 2014 ― የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ነገ ለሚያደርጉት ሕዝበ ውሳኔ በቂ ዝግጅት መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝበ ውሳኔ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ነጋሳን ጠቅሶ ኢቢሲ እንደዘገበው፣ ቦርዱ ለሕዝበ ውሳኔው ስኬት አስቀድሞ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።

የቦንጋ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከሳምንት በፊት መከፈቱን የገለጹት አስተባባሪው፣ ለሕዝበ ውሳኔው አስፈላጊ የሆኑ የምርጫ ሰነዶች ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ ለምርጫ ክልል ደርሰዋል ብለዋል።

በተዘጋጁት 22 የምርጫ ክልሎች በአምስት ዞኖች እና በአንድ ወረዳ ከዚህም በተጨማሪ ለምርጫ አፈጻጸም ሥራ ላይ የሚሳተፉ የምርጫ አስፈጻሚዎች ሙሉ በሙሉ ባለፉት ሳምንታት ውስጥ ሥልጠናዎች መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

በ22 የምርጫ ክልሎች 1 ሺህ 636 የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውንም ነው የገለጹት።

የሰነድ ስርጭት እስከ ምርጫ ጣቢያዎች መዳረሳቸውንም አቶ ሙሉጌታ አስታውቀዋል።

ከፀጥታ ጋር በተያያዘ እስካሁን ያጋጠመ ችግር የለም ብለዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ-ውሳኔ የኮንታ ልዩ ወረዳ፣ የምዕራብ ኦሞ ዞን፣ የቤንች ሸኮ ዞን፣ የካፋ ዞን፣ የዳውሮ ዞን እና የሽካ ዞን “ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል ወጥተው የጋራ አንድ ክልል መመሥረታቸውን እደግፋለሁ” እና “የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል አካል ሆነው መቀጠላቸውን እደግፋለሁ” በሚል የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img