አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 18፣ 2014 ― አሜሪካና የአውሮፓ ኅብረት ሕወሓትን እየደገፉ ነው ሲሉ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዑስማን ሳላህ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አስቀድሞ የተቀረፀ ነው በተባለ ቪድዮ መናገራቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ሳላህ ዩናትድ ስቴትስ አሜሪካና የአውሮፓ አጋሮቿ ህወሓትን የሚፈፅማቸውን ህገወጥ እና አደገኛ አመፅና ሁከት ከማወገዝ ይልቅ እተከላከሉለት ነው ሲሉ መውቀሳቸው በዘገባው ተመላክቷል።
ከዚህ ቀደም ዩናይትድ ስቴትስ በኤርትራ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ መጧሏ ይታወሳል፡፡
ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ በፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ተፈርሞ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ለግምዣ ቤቱ በተላለፈው የማስፈፀሚያ ትዕዛዝ አገሪቱ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ተጨማሪ የኤርትራ ባለሥልጣናትንም ያካተተ ማዕቀብ እጥላለሁ ማለቷ ይታወሳል።