Saturday, November 23, 2024
spot_img

በአራት ክልሎች ከ20 በመቶ በላይ በኮቪድ ቫይረስ የመያዝ ምጣኔ ተመዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 18፣ 2014 ― በኢትዮጵያ አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ የሆነው ዴልታ ቫይረስ በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራጨ በመሆኑ በአራት ክልሎች ከ20 በመቶ መሻገሩን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ በዛሬው እለት እንዳሳወቁት በሲዳማ 28 በመቶ፣ በአማራ 22 በመቶ፣ በኦሮሚያ 22 በመቶ እና በደቡብ 24 በመቶ የመያዝ ምጣኔ ተመዝግቧል፡፡

ዳይሬክተሯ በአገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 10 እስከ 16 ባለው ጊዜ ውስጥ ከተመረመሩት 57 ሺሕ 940 ሰዎች መካከል 8 ሺሕ 753 ሰዎች በቫይረስ የተያዙ ሲሆን፣ በአገር አቀፍ የመያዝ ምጣኔው ደግሞ 15 በመቶ ነው፡፡

በዚሁ ተመሳሳይ ሳምንት በአገር አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 ምክንያት በአጠቃላይ 271 ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ 175 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 45 ከኦሮሚያ፣ 25 ከአማራ፣18 ከደቡብ፣ 3 ከሲዳማ፣ 2 ከድሬዳዋ፣ 2 ከሐረሪ እና 1 ከቤኒሻንጉል ክልል መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህም ኮቪድ19 በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ከፍተኛ የሞት መጠን የተመዘገበት ሳምንት መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡

አሁን እየታየ ያለው የመያዝ፣ የሞት እና የጽኑ ሕሙማን ቁጥር መጨመር አዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ የሆነው የዴልታ ቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ መሆኑን እንደሚያመለክት የገለጹ ዶክተር ጽረዳ፣ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ያለመደረጋቸው እና የኮቪድ-19 ክትባት ሽፋን ዝቅተኛ መሆኑን እንደ ምክንያት ተጠቃሾች ጠቅሰዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ 14 ከተሞች ላይ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን (የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ፣ የእጅ መታጠብና ርቀትን መጠበቅ) በተመለከተ በተሰራው የምልከታ ደሰሳ ውጤት መሠረት በአብዛኛው ከተሞች ላይ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች ትግበራ ዝቅተኛ መሆኑ እና በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት እንዳለ ገልጸው ጥንቃቄው እንዲበረታ አሳስበዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img