Sunday, October 6, 2024
spot_img

ዶክተር እሌኒ ገብረመድኅን የተመድ ልማት ፕሮግራም ሹመት አገኙ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 18፣ 2014 ― ዶክተር እሌኒ ገብረመድኅን የተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም በአፍሪካ ቀጠና የሥራ ፈጠራ ዋና ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።

የተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም እንዳስታወቀው ከሆነ እሌኒ ገብረመድህን ‹‹ቲምቡክቱ›› የተባለውን በአፍሪካ የግል፣ የመንግስትና የወጣቶችን ጅምር የፈጠራ ሥራዎች በገንዘብ አቅርቦት የሚደግፍ አዲስ ፕሮግራምን ለማስጀመር ግምባር ቀደም ሚና ይጫወታሉ።

የአፍሪካን የወደፊት ተስፋ ለማሳደግ ዲጂታላይዜሽንን ማሳደግ እና ወጣቶችን ማበረታታት፤ በተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ተግባራት መካከል አንዱ እና ዋንኛው ነው።

በተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም በአፍሪካ ልማት ተጽዕኖ ፈጣሪ ቡድን አባል የሆኑት እሌኒ የፈጠራ መፍትሄዎችን በመንደፍና ተግባራዊ በማድረግ ከ25 ዓመታት በላይ ልምድ ያላቸው ኢትዮጵያዊት ናቸው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እሌኒ በአፍሪካ ልማት፣ በግብርና ገበያ፣ በሥራ ፈጠራ እና በወጣቶች የፈጠራ ችሎታ ላይ ከፍተኛ እውቅና፣ የተከበረ ድምጽና የአስተሳሰብ መሪነት ያላቸው ሴት ናቸው ሲልም እውቅናን ሰጥቷቸዋል።

እሌኒ ከአዲሱ ሀላፊነታቸው በፊት በግል እና የመንግስት ድርጅቶች ላይ በከፍተኛ የሥራ ሀላፊነቶች ያገለገሉ ሲሆን፣ በተለይም በኢትዮጵያ የወጣቶች መሪ ንግድ አፍላቂ፣ በብሉ ሞን፣ እንዲሁም በአፍሪካ ቀዳሚ የምርት ልውውጥ ገንቢ በሆነው በእሌኒ ኤል.ኤል.ሲ ውስጥ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ሰርተዋል።

እሌኒም በሦስት ዓመታት ውስጥ በዓመት 1.2 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ዋጋ በማስመዝገብ ከፍተኛ ዕውቅና የተሰጠው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ መሥራች እና የመጀመሪያ ሥራ አስፈፃሚም ነበሩ።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img