Thursday, December 5, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ በአየርላንድ የሚገኘው ኤምባሲዋን መስከረም 30 ልትዘጋ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 18፣ 2014 ― በአየርላንድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከመስከረም 30 ጀምሮ ሊዘጋ መሆኑን የአየርላንድ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል፡፡

ዘ ኢት አፍሪካን ይዞት እንደወጣው ዘገባ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በወሰኑት ውሳኔ ማዘኑን ገልጧል፡፡

አየርላንድ በቅርብ ጊዜያት በትግራይ ባለው ጦርነት ሰበብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ ላይ ማእቀብ እንዲጥል ግፊት ስታደርግ መቆየቷንና በዚህ የሁለቱ አገራት ግንኙነት መሻከሩም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡

በአየርላንድ የሚገኘውየኢትዮጵያ ኤምባሲ ሲዘጋ የልኡኩ አገልግሎት ወደ እንግሊዝ ለንደን ይዘዋወራል ተብሏል፡፡

ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር መጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ፣ ኢትዮጵያ በተለያዩ ሀገራት የከፈተቻቸውን ኢምባሲዎች የመቀነስ እቅድ አንዳላት መናገራቸውን ተከትሎ የኤምባሲዎች ቁጥር ማስተካከያ ማድረጉ እንደቀጠለ ይገኛል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img