አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ መስከረም 15፣ 2014 ― በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሹ ቅዳሜ ዕለት በፕሬዚዳንቱ መኖሪያ አቅራቢያ በሚገኝ መስቀለኛ መንገድ ላይ በአንድ የአጥፍቶ ጠፊ የመኪና ፍንዳታ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን አንድ ባለሥልጣን አስታውቀዋል።
በሞቃዲሾ የካምጃጃብ ዲስትሪክት ሃላፊ ሙአይዬ ሙደይ ለሮይተርስ እንደገለፁት በኤልጋአብ መስቀለኛ መንገድ ላይ በተጠመደ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ሰባት ሰዎች ሲሞቱ ስምንት ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል፡፡
ለጥቃቱ ተጠያቂው ማን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም የተባለ ቢሆንም ነገር መንግስትን ለመገልበጥ የሚፈልገው አልሸባብ በተደጋጋሚ እንደዚህ ዓይነት ፍንዳታዎችን እንደሚያካሂድ ዘገባው ጠቅሷል፡፡
በፍንዳታው ቦታ ላይ የአይን እማኝ ለየሮይተርስ እንደገለጸው በፍንዳታው ሰባት መኪኖች እና ሦስት አነስተኛ ተሽከርካሪዎችና ወድመው፣ መስቀለኛ መንገዱም በሙሉ በደም ተሸፍኗል።