Sunday, October 6, 2024
spot_img

በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ በአፍሪካ ኅብረት በኩል የሚደረጉ የማሸማገል ጥረቶችን እንደሚደግፍ ተመድ አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ መስከረም 15፣ 2014 ― የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ወደ ውይይት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ድርጅታቸው በአፍሪካ ህብረት በኩል ለሚደረጉ የማሸማገል ጥረቶች ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል፡፡

አንቶንዮ ጉቴሬዝ ይህንኑ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በተወያዩበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

በዚህ ውይይት ወቅት በዋናነት በውስጣዊ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች በተለይም የትግራይ ጉዳይ ላይ ትኩረት ተደርጎበት እንደተነሳ የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በውይይቱ በድጋሚ የሰላም ጥሪን አቅርበዋል ያለው ጽሕፈት ቤቱ፣ ሰብዓዊ ተደራሽነትን ይበልጥ ማጠናከር ይገባል ስለማለታቸው ገልጿል፡፡

በአሜሪካ ኒውዮርክ በመካሄድ ላይ ባለው 76ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ በመሳተፍ ላይ ያሉት አቶ ደመቀ፣ ከድርጅቱ ምክትል ዋና ፀሃፊ አሚና መሐመድ ጋርም በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img