Monday, September 23, 2024
spot_img

ሳዑዲ በአገሯ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው ልካ ስትጨርስ አዲስ ቪዛ መስጠት እንደምትጀምር አሳወቀች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ መስከረም 15፣ 2014 ― በርካታ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤቶቿ እንደሚሰቃዩ የሚነገርባት ሳዑዲ ዐረቢያ በአገሯ የሚገኙና መኖሪያ ፍቃድ የላቸውም ያለቻቸውን ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው መላኳን ካጠናቀቀች በኋላ አዲስ የስራ ቪዛ መስጠት እንደምትጀምር አስታውቃለች፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውኑን ወደ አገር ቤት እየሸኘች ያለችው አገሪቱ፣ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ከ45 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን መልሳለች፡፡

በሳዑዲ ይሰሩ የነበሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ወደ እስር ቤት የተወረሩ ሲሆን፣ አሁንም በርካታ ኢትዮጵያውያን ችግር ላይ እንዳሉ ይናገራሉ፡፡

የሳዑዲ መንግስት ወደ እስር ቤት ያስገባሁት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው እና በወንጀል የተጠረጠሩት ብቻ ናቸው ቢልም፣ የእስረኞች አያያዝን ጨምሮ እስሩ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም ያጠቃልላል የሚሉ ድምጾች ሲሰሙ ሰንብተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሳዑዲ አምባሳደር ሳሚ ቢን ጃሚል አብዱላህን በሳውዲ እስር ቤት ስላሉ ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ ጠይቄያለሁ ያለው አል ዐይን፣ በእስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው የመመለሱ ሂደት በቅርቡ ይጠናቀቃል እንዳሉት አስነብቧል።

በእስር ቤት ያሉ እና ወደ አገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያንን በነጻ ወደ አገራቸው በመመለስ ላይ ነን ያሉት አምባሳደሩ፣ በረራውን በሳዑዲ እና ኢትዮጵያ አየር መንገዶች በሳምንት ከ6 ጊዜ በላይ በረራዎችን እያካሄድን ነውም ብለዋል።

እነዚህን ዜጎች ወደ አገራቸው የመመለሱ ተግባር እንደተጠናቀቀ አዲስ የስራ ቪዛ በሳዑዲ አረቢያ ከተሞች መስራት ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን መሰጠት ይጀመራልም ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img