Sunday, October 6, 2024
spot_img

በጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ መገንባት በተመለከተ መንግሥት ከተመድ ጋር መከረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ መስከረም 14፣ 2014 ― በኢትዮጵያ በጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ መገንባት በተመለከተ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ ከተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ጄኔ መሐመድ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

በኒውዮርክ የመንግስታቱ ድርጅት ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደው በዚህ ምክክር ላይ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ መሰረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ለመገንባት መንግስት በላቀ አጋርነት ከተ.መ.ድ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መግለጻቸውን ጽሕፈት ቤታቸው አሳውቋል፡፡

አቶ ደመቀ በአሁን ጊዜ አገሪቱ እየገጠሟት ካሉት የፀጥታ ችግሮች ጋር በተያያዘ የመልሶ ማቋቋም እና የመልሶ ማልማት ተልዕኮን ለማስፈፀም በተመድ በኩል የበለጠ ትብብር እና ድጋፍ እንጠብቃለን ማለታቸውም ተመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ልዑካንን ጨምሮ ከመላው ዓለም የተውጣጡ መሪዎች የተገኙበት 76ኛው የመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከሰሞኑ እየተካካደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img