አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ መስከረም 14፣ 2014 ― የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የተመረጡ የአፍሪካ አገራት የሚያደርገውን የገንዘብ ድጎማ ለመቀነስ መወሰኑ አስወቅሶታል፡፡
የዩኬ ፓርላማ ኮሚቴ የአገሪቱ መንግሥት ለተወሰኑ የአፍሪካ አገራት የሚሰጠውን ድጎማ ለመቀነስ መወሰኑ ‹‹ግብዝነት ነው፤ እጅግም ያስቆጣል›› ሲል ኮንኖታል።
ኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት የተባለው ኮሚቴ፤ በተለይም በግጭት እየተናጡ ከሚገኙት የምሥራቅ አፍሪካ አገራት በግማሽ ወይም ከዚያም በላይ ድጎማ መቀነሱ አግባብ እንዳልሆነ አስታውቋል።
ይህ የዩኬ ፓርላማ ኮሚቴ አገሪቱ የምታደርጋቸው ልገሳዎች ላይ ትችት በመሰንዘር የሚታወቅ መሆኑን ያመለከተው የአገሩ የሚዲያ ተቋም ቢቢሲ፣ አሁንም ኮሚቴው ለኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሞዛምቢክ፣ ሶማሊያ እና ሌሎች የአፍሪካ አገራት የሚሰጠው ድጎማ መቀነሱ ተገቢ አይደለም ማለቱን አስነብቧል፡፡
የዩኬ መንግሥት በበኩሉ ከአፍሪካ አገራት ድጎማ ለመቀነስ የወሰነው ኮሮና ቫይረስ ባሳደረበት ተጽእኖ ምክንያት መሆኑን አስታውቋል።
ኮሚቴው ግን ሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ የሚገኙት አገራት ከመቼውም በላይ የዩኬን እርዳታ በሚፈልጉበት በዚህ ጊዜ ድጋፍ ለመቀነስ መወሰኑን ተችቷል።
እነዚህ የቀጠናው አገራት ከገቡበት የሰብአዊ ቀውስ ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥ ካስከተለው ችግርም ጋር እየታገሉ በመሆኑ ድጎማ መቀነስ እንዳልነበረበት ኮሚቴው ገልጿል።
የኢንተርናሽናል ዴቨሎፕመንት ኮሚቴ ኃላፊዋ ሳራ ቻምፒዮን