Sunday, October 6, 2024
spot_img

በታላቁ አርበኛ ደጃዝማች ዑመር ሰመተር የሚጠራ ት/ቤት ዳግም ተሠየመ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ መስከረም 14፣ 2014 ― በአዲስ አበባ ከተማ በታላቁ የኢትዮጵያ አርበኛ ደጃዝማች ዑመር ሰመተር የሚጠራ ትምህርት ቤት ዳግም ተሠይሟል።

በጀግናው ሥም እንዲጠራ የተሠየው ትምህርት ቤት በከተማው ኮልፌ አጠና ተራ እፎይታ የገበያ ማዕከል አካባቢ ይገኝ የነበረው እፎይታ ት/ቤት ነው።

ትምህርት ቤቱ በአዲሱ ሥያሜው ደጃዝማች ዑመር ሰመተር ስም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በሚል እንዲጠራ በተወሰነበት ሥነ ሥርዐት ላይ የደጃዝማች ዑመር ሰመተር የልጅ ልጆቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው እንደተገኙ ታውቋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በደጃዝማች ዑመር ሰመተር ሥያሜ ይጠራ የነበረው በመርካቶ አንዋር መስጂድ ጀርባ ይገኝ የነበረው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በልማት ምክንያት መፍረሱ ይታወቃል።

በኦጋዴን ካልካዩ በተባለች ቦታ 1871 የተወለዱት ታላቁ ጀግና ደጃዝማች ዑመር ሰመተር፣ ለኢትዮጵያ ነፃነት ከወራሪው የፋሽስት ኢጣሊያ ጦር ጋር ከተዋደቁት ጀግኖች አርበኞች አንዱ ናቸው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img