Sunday, September 22, 2024
spot_img

እርዳታ ጭነው ትግራይ የገቡ ተሽከርካሪዎችን ለመመለስ የነዳጅ እጥረት መኖሩን ሹፌሮቹ መናገራቸውን የመንግስታቱ ድርጅት እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ መስከረም 14፣ 2014 ― ከቀናት በፊት የእርዳታ ቁሳቁስ ጭነው ወደ ትግራይ ክልል ከገቡ በኋላ ሳይመለሱ የሚቀሩ ከባድ የጭነት ተሸከርካሪዎች ጉዳይ አሳስቦኛል ያለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ተሸከርካሪዎቹን ለመመለስ የነዳጅ እጥረት መኖሩን ሹፌሮቹ አመልክተዋል ብሏል፡፡

የድርጅቱ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ባወጣው መግለጫ፣ ከነዳጅ እጥረት በተጨማሪ ከሰመራ ወደ መቐለ ባቀኑበት ወቅት ደርሶብናል ያሉት እንግልት፣ ዝርፊያ እና ሌሎችም ስጋት ውስጥ እንደከተታቸው ጠቋሟል፡፡

የተሽከርካሪዎቹ ከክልሉ አለመመለስ አሳስቦኛል ያለው የመንግሥታቱ ድርጅት፣ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚያስፈልገውን ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ የጭነት ተሽከርካሪዎቹ ያስፈልጉኛል ማለቱ አይዘነጋም፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ስለ ጉዳዩ ከመግለጹ ቀደም ብሎ የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ሥዩም በሰጡት መግለጫ ትግራይ ከገቡት ተሸከርካሪዎች መካከል 428ቱ ከክልሉ ተመልሰው አለመውጣቸውን አሳውቀው ነበር፡፡

ጉዳዩ በመንግሥታቱ ድርጅት ጽሕፈት ቤት የትዊተር ገጽ ይፋ በተደረገበት ወቅት ከቅሬታ ስር ምላሽ የሰጡት የሕወሃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አሁን የመንግስታቱ ድርጅት ሾፌሮቹ አቅርበውታል ካለው የነዳጅ አቅርቦት እና የፀጥታ ስጋት በተጨማሪ በአፋር ለወራት መሰለፋቸውን ዘርዝረው ጉዳዩ ከኛ ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img