Saturday, November 23, 2024
spot_img

ፈረንሳይን ጨምሮ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምን ለዓለም ጤና ድርጅት አለቃነት እጩ አደረጉ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ መስከረም 14፣ 2014 ― የአውሮፓ ኅብረት አገራት የሆኑት ፈረንሳይ እና ጀርመንን ጨምሮ ሌሎችም የኅብረቱ አባል አገራት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምን የዓለም ጤና ድርጅት አለቃ እንዲሆኑ እጩ አድርገው አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ ግንቦት ወር ለሚካሄደው የድርጅቱ አለቃነት ምርጫ ምርጫ አገራቱ ዶክተር ቴድሮስን እጩ አድርገው ማቅረባቸውን በጄኔቫ የጀርመን ልኡክ ተናግረዋል፡፡

ከሦስት ቀናት በፊት የጀርመን ጤና ሚንስትር ጀንስ ሳፕሃን በተመሳሳይ የዶ/ር ቴድሮስን ዳግም መመረጥ ጀርመን እንደምትደግፍ ገልጸው፣ ሌሎች አገራትም ለቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጠይቀው ነበር፡፡

እጩ ተደርገው የቀረቡት ዶ/ር ቴድሮስ ምንም እንኳን በይፋ ለሁለተኛ ዙር እንደሚወዳደሩ ይፋ ባያደርጉም፣ እጩ ሆነው መቅረባቸውን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበው ነበር፡፡

አገራት በቀጣይ የዓለም ጤና ድርጅትን የሚመራ ግለሰብ የሚጠቁሙበት ጊዜ በትላንትናው እለት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ሌላ እጩ ስለመቅረቡ የተነገረ ነገር የለም፡፡

የአውሮፓ አገራት ለዶ/ር ቴድሮስ ሁለተኛ ዙር መመረጥ ድጋፉን ይስጥ እንጂ የዶ/ር ቴድሮስ ዳግም መመረጥን የሚቃወሙም ድምጾች ይሰማሉ። ከሚቃወሟቸው መካከል የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹሙ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በአንድ ወቅት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊን ‹‹ወንጀለኛ ነው›› ሲሉ ተናግረው ነበር። ጀነራሉ ዶክተር ቴድሮስ ወንጀለኛ ነው ያሉት በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ የዓለም አቀፍ ተልዕኮ ዕድላቸውን ተጠቅመው የሕወሓት ቡድንን ለመርዳት ጥረት ማድረጋቸውን በማንሳት ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img