Saturday, September 21, 2024
spot_img

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የሽግግር አስተዳደር ምስረታን እንደ አማራጭ አቀረበ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 13፣ 2014 ― በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ክልላዊ የሽግግር መንግሥትን ጨምሮ ጊዜያዊ አስተዳደርና ባለአደራ መንግሥት በክልሉ እንዲመሰረት የሚሉ አማራጮችን አቅርቧል፡፡

ፓርቲው ለዚህም እንደ ምክንያትነት የጠቀሰው በክልሉ በተወሰኑ ቦታዎች ምርጫ ካለመደረጉ ጋር ተያይዞ “የአመራር ክፍተት እንዳይፈጠር” በማለት መሆኑን ነው ያስታወቀው፡፡

ባለፈው ዓመት ሰኔ 14 ብሔራዊ ምርጫ ቢካሄድም በክልሉ በመተከል፣ በካማሽ እና በከፊል አሶሳ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ ምርጫ አልተደረገም።

የክልሉ ገዢ ፓርቲ ብልጽግና ለዚህ ጥያቄ በሰጠው ምላሽ ያለው ብቸኛ አማራጭ በምርጫ ቦርድ በሚወጣ መርሃ ግብር መሰረት በሚደረግ ምርጫ እንጂ በሌላ መልኩ የሚቋቋም አስተዳደር እንደማይኖር አመልከቷል።

በክልሉ ሊደረግ የነበረውና በድጋሚ የተራዘመው ምርጫ መስከረም 20 ሊከናወን ቢታሰብም ያለው የጸጥታ ሁኔታ ባለመሻሻሉ ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መስከረም 20/2014 በክልሉ ምርጫ እንዳይደረግ መወሰኑን ገልጿል።

ፓርቲው የክልሉን ሕገ መንግሥት ጠቅሶ በክልሉ ምክር ቤት አብላጫ ወንበር ያለው ፓርቲ መንግሥት እንደሚመሰርት ቢደነግግም ምርጫ ተደርጎ አብላጫ ወንበር ያገኘ ፓርቲ የለም ብሏል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ክልሉን ከ2007 ጀምሮ ሲያስተዳድር የነበረው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ከመስከረም 2014 ጀምሮ የሥልጣን ጊዜው ስለሚመጠናቀቅና በተወሰኑ ቦታዎችም ምርጫ ባለመደረጉ ገዢው ፓርቲ ስልጣን ላይ ለመቆየት ሕጋዊ መሰረት የለውም ብሏል።

የምክር ቤቱ ስልጣን በ2012 ቢጠናቀቅም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በተሰጠው ውሳኔ ሥልጣኑ እስከ መስከረም 24/2014 ለአንድ ዓመት መራዘሙንም አስታውሷል።

ነገር ግን ከመስከረም 25 ጀምሮ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሥልጣን ላይ መቆየት እንደሌለበት፣ ፓርቲው በሕዝብ ሳይመረጥ ክልሉን ማስተዳደር እንደማይችልና ድጋሚም የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ማድረግና የሥልጣን ጊዜ ማራዘም አይቻልምም ብሏል።

ስለዚህም ምርጫ ተካሂዶ ክልላዊ መንግሥት እስኪቋቋም ድረስ የክልሉ ገዢ ፓርቲ እና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ ክልላዊ የሽግግር አስተዳደር እንዲመሰርቱ ጥሪው አቅርቧል።

ፓርቲው በሁለተኛ ደረጃ ፓርቲው ያቀረበው አማራጭ ሃሳብ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም የሚል ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img