Sunday, October 6, 2024
spot_img

ኢትዮ ቴሌኮም በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት 5ጂ ኔትዎርክን ለሙከራ አስጀምራለሁ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 13፣ 2014 ― ኢትዮ ቴሌኮም በማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ያስጀመረውን የ4ጂ ኤል.ኢ.ቲ አድቫንስድ በደብረ ብርሃን ከተማ አስመርቋል።

ኔትዎርኩ የተመረቀበት የማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ፍቼ፣ ደብር ብርሃን እና ሸዋ ሮቢት ጨምሮ 7 ከተሞች ያካትታል። በምርቃቱ ስነስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉ የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ አሁን የተመረቀው የ4ጂ ኤል.ኢ.ቲ አድቫንስድ ከ3ጂ በ13 እጥፍ ፈጣን እንደሆነ አስታወቀዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በመጀመሪያ ዙር ማስፋፊያው ከ100 በላይ ከተሞችን እንደሚያካትት ተገልጿል። አሁን ላይም በኢትዮ ቴሌኮም አደረጃጀት መሰረት የ4ጂ ኤል.ኢ.ቲ አድቫንስድ ያልጀመረው በአንድ ሪጅን ብቻ መሆኑን ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።

ፍሬህይወት ኢትዮ ቴሌኮም በአውሮፓውያኑ 2022 5ጂ ኔትዎርክን ለሙከራ እንደሚያስጀምረ አስታውቀዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img