Sunday, October 6, 2024
spot_img

31 መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በትግራይ ረሃብና ጦርነት እንዲቆም ለተመድ ደብዳቤ ፃፉ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 13፣ 2014 ― በትግራይ ጦርነትና ረሃብ እንዲቆም እርምጃ መወሰድ አለበት በሚል 31 ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝና ለድርጅቱ የጸጥታው ምክር ቤት አባል አገራት ተወካዮች ደብዳቤ አስገብተዋል።

ድርጅቶቹ በሠሜን ኢትዮጵያ የተከሰተው ጦርነት እንዲቆምና በረሃብ አፋፍ ላይ የሚገኙ ሚሊዮኖችን እርዳታ እንዳይደርስ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ ጠይቀዋል።

ደብዳቤው ግሎባል ሴንተር ፎር ዘ ሪስፖንሲቢሊቲ ቱ ፕሮቴክት በሚል ድረ-ገፅ የወጣ ሲሆን፣ ከድርጅቶቹም መካከል አክሰስ ቡክስ፣ አሊያንስ ፎር ፒስ ቢዩልዲንግ፣ አሶሺየሽን ኦፍ ኮንሰርድ አፍሪካ ስኮላርስ፣ ሲቪል ሶሳይቲ አክሽን ኮሚቴ፣ ኤጁኬተርስ ኢንስቲትዩት ፎር ሂውማን ራይትስ፣ ኢትዮፕያን ኮሚዩኒቲ ዴቨሎፕመንት ካውንስል ይገኙበታል።

ዋና ፀሐፊው በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤትን ጨምሮ በአፍሪካ ሕብረትና በሌሎች መድረኮች ላይ የትግራይ ቀውስ ላይ ትኩረት እንዲሰጡትና የግጭቱ ተሳታፊ አካላትንም በማሳተፍ በአስከፊነቱ ከ1977 በኋላ የታየውን እየጨመረ ያለውን ረሃብ መከላከል እንዲቻል መደረግ አለበት ብለዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img