Saturday, September 21, 2024
spot_img

ራሚስ ባንክ በቂ ሐብት በማሰባሰቡ ወደ ምሥረታ ተሸጋገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 13፣ 2014 ― በምሥረታ ሒደት 2 አመታትን ያስቆጠረውና ሙሉ ለሙሉ የወለድ አልባ አገልግሎት የሚሠጠው ራሚስ ባንክ በቂ ሐብት በማሰባሰቡ ወደ ምሥረታ መሸጋገሩ ታውቋል፡፡

ባለፈው ሚያዝያ ብሔራዊ ባንክ ባስተላለፈው ትእዛዝ በምስረታ ላይ የሚገኙ ባንኮች 500 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ይዘው እና የመስራች ጉባኤ አድርገው እስከ ጥቅምት 2 ለፈቃድ እንዲያመለክቱ ቀነ ገደብ ማስቀመጡ ይታወሳል።

በዚህም ራሚስ 724 ሚሊዮን ብር በመሰብሰብ እውን ለመሆን ተቃርቧል የተባለ ሲሆን፣ መስከረም 22 የመስራች ጉባኤ ለማድረግ ማቀዱንም ካፒታል ዘግቧል፡፡

ራሚስ ባንክ ባንኩን ለማቋቋም ከሚጠበቅበት የ500 ሚሊዮን ብር ካፒታል ማሟላቱን ከማረጋገጡ በፊት በተመሳሳይ ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ ባንክ ለመመሥረት የአክሲዮን ሽያጩን ሲያካሂድ ከነበረው ዛድ ባንክ ጋር ለመዋሃድ የሚያስችለውን ስምምነት ለመፈራረም በዝግጅት ላይ ነበር፡፡

የባንኩ አደራጆች ባንካቸው ራሱን ችሎ ባንክ ለማቋቋም የሚያስችለውን ካፒታል ቢያሟላም ከዛድ ባንክ ጋር ለመዋሃድ የተደረሰው ስምምነት እንደሚቀጥል ከዚህ ቀደም አሳውቀው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img