Sunday, October 6, 2024
spot_img

በሲዳማ ክልል ከተማዎች የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች በኃይል እየታፈሱ መሆኑ ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 13፣ 2014 ― የሲዳማ ክልል ሐዋሳን ጨምሮ በተለያዩ ከተማዎች የሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች በኃይል እየታፈሱ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት እየተላኩ መሆናቸው የሚያመለክት መረጃ ወጥቷል፡፡

ከከተሞች በተጨማሪም የገጠር ወጣቶችም ወዴት እና ለምን እንደሚሄዱ በቂ መረጃ ሳይሰጣቸው ከየወረዳው እየተለቀሙ መሆኑን ማለዳ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ይህንኑ ተከትሎም ልጆቻቸው የታፈሱባቸው ቤተሰቦች በከተማው መታየታቸውንም ማለዳ በፎቶ አስደግፎ መረጃ አውጥቷል፡፡

በጉዳዩ ላይ የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ያሳወቀው ነገር ስለመኖሩ የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

ፎቶ፡ የቤተሰብ አባላቸው ታፍሰውባቸዋል የተባለ
የፎቶ ምንጭ፡ ማለዳ ሚዲያ

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img