Friday, November 22, 2024
spot_img

በባሕር ዳር ከተማ ከፀጥታ ኃይሎች ውጭ ማንኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ተከለከለ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 12፣ 2014 ― የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት ከፀጥታ ኃይል ውጭ ማንኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደተከለከለ አሳውቋል።

ቀደም ሲል የሕወሃት ኃይል “በክልሉ ሰርጎ በመግባት በየከተሞች የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቆጣጠር ተብሎ ተጥሎ የነበረውን የሰዓት እላፊን እና ሌሎች የተለያዩ ውሳኔዎችን በከተማው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች እንዳይስፋፉ ማስተካከያ” መደረጉን ያስታወሰው ምክር ቤቱ፣ ነገር ግን በክልሉ ተጋርጧል ያለውን “የህልውና ጉዳይ” ያልተገነዘቡ ያላቸው አካላት ለከተማው የማይመጥን አንዳንድ ህገ ወጥ እንቅስቃሴዎች እያደረጉ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ምክር ቤቱ ከጦር መሳሪያ ክልከላ በተጨማሪ ለንግድ ስራ ከተፈቀደላቸው ቦታ ውጭ የእግረኛና የተሽከርካሪ መንገድ ዘግቶ መጠጥ ቤት ማስተናገድ፣ ኮበልስቶን መንገዶችን ዘግቶ ማንኛውንም ግብይት መፈፀም በጥብቅ ከልክሏል። ከዚህ ውጭ በከተማው በተናጥልም ሆነ በቡድን የተደራጀ የትኛውንም ህጋዊም ይሁን ህጋዊ ያልሆነ የውርርድና የቁማር ቤት ከፍቶ መጫዎት እና ማጫዎት፣ በመንግስት ከተፈቀደለት ተቋም ውጭ ምንም አይነት ወታደራዊ ስልጠና መሰልጠንና ማሰልጠን እና በመጠጥ ቤቶች አካባቢ ነዋሪዎችን የሚረብሽ ሁከትና ግርግር በመፍጠር ለሰላማዊ ነዋሪዎች ስጋት መሆን እና ተዛማጅ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ከልክሏል።

ከላይ የተገለጹትን ውሳኔዎች ተላልፎ የሚገኝ አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰድ እንደሚቻል የፀጥታ ምክር ቤቱ አሳውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img