Sunday, October 6, 2024
spot_img

ኢትዮጵያ ያቀረበችው የብድር ይራዘምልኝ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ ማግኘቱን የገንዘብ ሚኒስቴር አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 12፣ 2014 ― ኢትዮጵያ በቡድን 20 የጋራ የብድር ማዕቀፍ ስር ያሉባትን ብድሮች እንዲራዘሙላት ያቀረበችው ጥያቄ አወንታዊ ምላሽ ማግኘቱ ተገልጧል፡፡

ኢትዮጵያ ባሳለፍነው አመት የካቲት ወር ያቀረበችውን ጥያቄ አስመልክቶ የብድር ሰጪ ሃገራት ኮሚቴ መስከረም 6፣ 2014 ለመጀመርያ ጊዜ ስብሰባ በመቀመጥ እንደተወያዮበትና ምላሻቸው በጎ የሚባል እንደሆነ ነው የገንዘብ ሚኒስቴር የገለፀው።

ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ዛሬ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ በፈረንሳይ እና በቻይና የተመራው ስብሰባ ኢትዮጵያ በኮቪድ እና በሀገሪቱ ባለው ግጭት ሳቢያ ያለችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባቱ ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን፣ የመጨረሻ ውሳኔውን እና ቀጣይ ሁኔታዎችን ኮሚቴው በቀጣይ ሳምንታት እንደሚያሳውቅም ገልጿል።

ኢትዮጵያ ለአበዳሪ ሀገራቱ ያቀረበችውን ጥያቄ በማስመልከት የአለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ (አይ ኤም ኤፍ) ቃል አቀባይ ጌሪ ራይስ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ባወጡት መግለጫ ኮሚቴው መልስ እንዲሰጥበት አሳስበው ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img