Sunday, September 22, 2024
spot_img

ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ለሁለተኛ ዙር ምርጫ የጀርመንን ድጋፍ አገኙ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 12፣ 2014 ― ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ለሁለተኛ ዙር የዓለም ጤና ድርጅትን በዋና ኃላፊነት እንዲመሩ የጀርመን መንግሥትን ድጋፍ ማግኘታቸው ተዘግቧል።

የጀርመን ጤና ሚንስትር ጀንስ ሳፕሃን የዶ/ር ቴድሮስን ዳግም መመረጥ ጀርመን እንደምትደግፍ ገልጸው፣ ሌሎች አገራትም ለቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

“አጋር አገራት ዋና ኃላፊ ቴድሮስን እንዲያጩ እንጋብዛለን” ሲሉ የጀርመን ጤና ሚንስትር ጀንስ ሳፕሃን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ ለጋሽ ከሆኑ አገራት አንዷ የሆነችውን የጀርመን ድጋፍ ማግኘታቸው ዳግም የመመረጥ እድላቸውን ከፍ ያደርጋል ተብሏል።

ዶ/ር ቴድሮስ ምንም እንኳን በይፋ ለሁለተኛ ዙር እንደሚወዳደሩ ይፋ ባያደርጉም፣ ሮይተርስ የዜና ወኪል የዓለም ጤና ድርጅትን ለመምራት እጩ ሆነው መቅረባቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር።

አገራት በቀጣይ የዓለም ጤና ድርጅትን የሚመራ ግለሰብ የሚጠቁሙበት ጊዜ በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል።

የጀርመን መንግሥት ለዶ/ር ቴድሮስ ሁለተኛ ዙር መመረጥ ድጋፉን ይስጥ እንጂ የዶ/ር ቴድሮስ ዳግም መመረጥን የሚቃወሙም ድምጾች ይሰማሉ።

ከሚቃወሟቸው መካከል የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹሙ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ በአንድ ወቅት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊን “ወንጀለኛ ነው” ሲሉ ተናግረው ነበር።

ጀነራሉ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም አቀፍ ተልዕኮ ዕድላቸውን ተጠቅመው የሕወሓት ቡድንን ለመርዳት ጥረት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img