Sunday, October 6, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ ቮዳኮም ከሳፋሪኮም ተጨማሪ ድርሻ ሊገዛ ነው

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 11፣ 2014 ― የደቡብ አፍሪካው የቴሌኮም ኩባንያ ቮዳኮም በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ በተሠማራው ሳፋሪኮም ኩባንያ ተጨማሪ የ10 ነጥብ 9 በመቶ ድርሻ ሊገዛ መሆኑን የኬንያው ቢዝነስ ዴይሊ ጋዜጣ ዘግቧል።

ቮዳኮም በ1 ነጥብ 74 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ድርሻውን የሚገዛው ከሌላኛው ባለድርሻ ከእንግሊዙ ሲዲሲ ግሩፕ መሆኑ ነው የተገለጸው።

ቮዳኮም የተጠቀሰውን ድርሻ ከገዛ፣ በኢትዮጵያው ሳፋሪኮም ያለው ድርሻ ከ6 ወደ 17 በመቶ ያድጋል።

በኬንያው የሳፋሪኮም ገበያ የ35 በመቶ ድርሻ ያለው ቮዳኮም ድርሻውን ለማሳደግ መወሰኑ፣ ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በሚጀምረው የቴሌኮም አገልግሎት አዋጭነት ላይ ከፍተኛ መተማመን እንዳሳደረ ያሳያል ተብሏል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img