Tuesday, December 3, 2024
spot_img

ኢዜማ እና የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲዎች በሶማሌ ክልል ከሚካሄደው ምርጫ ራሳቸውን አገለሉ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 11፣ 2014 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እና የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲዎች (ነእፓ) ፖለቲካ ፓርቲዎች “ከዚህ ቀደም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረብናቸው ቅሬታዎች ሊፈቱ ባለመቻላቸው የምርጫውን ሂደት ተዓማኒነት ጥርጣሬ ውስጥ ያስገባል” በማለት መስከረም 20 በሶማሌ ክልል ከሚካሄደው ምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን አሳውቀዋል።

ፓርቲዎቹ ተሰርቆ የነበረው የምርጫ ቁሳቁስ በአዲስ አለመተካቱ፣ በየደረጃው መዋቀር የነበረበት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መዋቅር ከመንግሥት መዋቅር ጋር የተዋሀደ መሆኑ፣ የምርጫውን ሂደትና የጊዜ ሰሌዳ በአግባቡ አለማስቀመጥ፣ በተጨማሪም አሁንም በዚያው ሂደት የቀጠለ በመሆኑ፤ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የሠለጠኑ ሠልጣኞች ሳያውቁ የምርጫ ቁሳቁስና ሰነድ በወረዳና በቀበሌ የመንግሥት መዋቅር ሠራተኞች እጅ በመግባቱ እና ባለው የመረጃ ክፍተት ምክንያት ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ለእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ምን ያህል የመራጮች ካርድ እንደመጣ ግልጽ አለመሆኑን በመጥቀስ በምርጫው ያለመሳተፍ ውሳኔያቸውን ገልጸዋል።

የኢዜማ ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ የሶማሌ ክልል አባላቱን ውሳኔ መቀበሉን የኢዜማ ምርጫ እና ስትራቴጂክ ክፍል አባል የሆኑት አቶ እዮብ መሳፍንት ነግረውኛል ብሎ አዲስ ዘይቤ ዘግቧል።

በክልሉ ምርጫ የሶማሌ ብሔራዊ ነጻነት ግንባር በተመመሳይ ራሱን ማግለሉን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img