Sunday, October 6, 2024
spot_img

ፖሊስ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ448 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ያዝኩ አለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 11፣ 2014 ― የፌደራል ፖሊስ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ448 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር በቁጥጥር ሥር አዋልኩ አለ።

ፌደራል ፖሊስ ዛሬ እንዳስታወቀው መነሻውን ደብረ ብርሃን ከተማ ያደረገው ተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪ አዲስ አበባ ከደረሰ በኋላ ወደ ሀረር ከተማ ለመጓዝ ቃሊቲ ኬላ ላይ በተደረገበት ፍተሻ 448 ሺህ 550 ዶላር ይዣለሁ ብሏል።

ግምቱከ20 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመተውን የአሜሪካ ዶላር ሲያዘዋውር የነበረውን አሸከርካሪንም መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረውን ገንዘብ ሊይዝ የቻለው በደረሰው ጥቆማ መሠረት ባደረገው ፍተሻ አሽከርካሪው ዶላሩን በቢራ ሳጥን ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር ነው።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img