Sunday, October 6, 2024
spot_img

ዓለም አቀፍ ተቋማት በአማራ ክልል በችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች በአፋጣኝ እንዲደርሱ የሚጠይቅ ሠልፍ ተካሄደ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 11፣ 2014 ― በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ፣ ዋግህምራ እና ሌሎች አካባቢዎች በችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ዓለም አቀፍ ተቋማት በአፋጣኝ ሊደርሱላቸው ይገባል ሲሉ በአዲስ አበባ የሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጆች ጠይቀዋል፡፡

የክልሉ ተወላጆች አዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጽሕፈት ቤት በር ላይ ዛሬ ማለዳ በመገኘት የተቋውሞ ድምፃቸውን ማሰማታቸውን የፎቶ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በሰልፉ ላይ ‹‹የዓለም ዐቀፍ ተቋማት በትግራይ ክልል ውስጥ ገብተው ድጋፍ እንዳደረጉት ሁሉ፤ በአማራ ክልልና በአፋር ክልልም በችግር ውስጥ ላሉ ዜጎች ሊደርሱላቸው ይገባል›› የሚል መፈክር ተስተጋብቷል፡፡

ሠልፈኞቹ በሰሜን ወሎ፣ በሰሜን ጎንደር፣ በዋግምራ፣ በመርሳ፣ በቆቦና መሰል በአማራ ክልል በሚገኙ አካባቢዎች ላሉ ዜጎች የመድኃኒት እና የምግብ ድጋፍ ሊያደርስላቸው ይገባልም ብለዋል።

አንዳንድ ተቋማትን በስም በመጥቀስም በእነዚህ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ምንም ዓይነት ድጋፍ ሲያደርጉ አላስተዋልንም ብለዋል፡፡ ሰልፈኞቹ ከጠቀሷቸው የረድኤት ተቋማት መካከል የአሜሪካው የረድኤት ድርጅት ዩኤስኤአይዲ፣ የአለም የምግብ ፕሮግራም እና የተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት ይገኙበታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img