አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 10፣ 2014 ― በትግራይ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች ከትግራይ ውጪ ባሉ መጠለያዎች እንዲዛወሩ የሚጠይቅ ሰልፍ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ተደርጓል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ደጃፍ በተደረገው ሰልፍ በትግራይ ክልል ማይ ዐይኒ እና አዲ ሀሩሽ የሚገገኙትን ኤርትራዊያን ፀጥታው የተረጋገጠ ሥፍራ እንዲዛወሩ ተጠይቋል።
በተጨማሪም ሰልፈኞቹ በአዲስ አበባና እና ግጭቱ በተስፋፋባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ስደተኞችም ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ጥሪ አቅርበዋል።