Sunday, October 6, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጣ የደህንነት ስጋትን መቀልበስ የሚያስችል የመከላከያ ደህንነት ስትራቴጂ ተዘጋጅቷል ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 10፣ 2014 ― በኢትዮጵያ ላይ ከማንኛውም አቅጣጫ ሊቃጣ የሚችል የደህንነት ስጋትን መቀልበስ የሚያስችል የመከላከያ ደህንነት ስትራቴጂ መዘጋጀቱን የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነዓ ያደታ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሩ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች፣ አምባሳደሮችን ፣ዲፕሎማቶች፣ ተጠሪ ተቋማት ፣ከመከላከያ ሚኒስቴር እና ከኤምግሬሽ ለተውጣጡ ሰራተኞች በውጭ ጉዳይ ግንኙነትፖሊሲ እና በመከላከያ ደህንነት ስትራቴጂ ዙሪያ ያተከረ ሥልጠና ላይ ነው ይህንን ያስታወቁት።

ዶክተር ቀንዓ ያደታ፤ ስትራቴጂው ሲዘጋጅ ከዲፕሎማሲው እና ከዓለም አቀፍ ግንኙነት የኢትዮጵያ መርሆች ጋር በተገናዘበ መንገድ መሆኑን እንደገለጹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

በመከላከያ ሚኒስቴር የዉጭ ግንኘነት ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ በበኩላቸው፤ አዲሱ የመከላከያ ደህንነት ስትራቴጂ ከአሁን በፊት ያልነበሩ የባህር እና የሳይበር አውዶችን ያካተተ መሆኑን አብራርተዋል ።

የተሻሻለው የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ፖሊሲም ከመጽደቁ አስቀድም ግብዓት እና አስተያየት እንዲሰጥበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን አስተያየት እንደተሰጠበት ታውቋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img