Sunday, October 6, 2024
spot_img

በቆቦና ዙሪያው በሕወሃት ኃይሎች እንደተፈፀመ የሚነገረው የንጹሐን ጥቃት እንዳሳሰበው ኢሰመኮ ገለፀ

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ መስከረም 9፣ 2014 ― የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በቆቦ ከተማና በዙሪያው ካሉ የገጠር ቀበሌዎች በሕወሃት ኃይሎች እንደተፈፀመ የሚነገረው የንጹሐን ጥቃት እንዳሳሰበው ገልጿል።

ኮሚሽኑ የሲቪል ዜጎች መኖሪያ አካባቢዎችን፣ ቤት ለቤት ሐሰሳና ግድያ፣ ዝርፊያና የሲቪል መሰረተ ልማቶች ጥቃት ጭምር መፈፀሙን ሪፖርቶች ደርሰውኛል ብሏል።

በጥቃቶቹ ላይ የሚያደርገው ምርመራ እንደሚቀጥል ያመለከተው ኢሰመኮ፣ በግጭቱ የሚሳተፉ አካላት በማንኛውም ወቅት ሲቪል ሰዎችን የመጠበቅ ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img