Sunday, October 6, 2024
spot_img

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በገባችበት የድንበር ውዝግብ የቱርክን አሸማጋይነት መቀበሏ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ መስከረም 9፣ 2014 ― በትግራይ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ ጦሯን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ያስጠጋችው ሱዳን ውዝግቡን ለመፍታት በቱርክ የቀረበውን የሽምግልና ጥያቄ መቀበሏ ተሰምቷል።

ይህንኑ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መርየም ሳዲቅ አል መህዲ ለመገናኛ ብዙኃን መናገራቸውን ሁሪያት በድረ ገጹ አስነብቧል።

የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት መሪው ዐብዱልፈታህ አል ቡርሃን ባለፈው ወር ወደ ቱርክ ማቅናታቸውን ያስታወሱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ፣ በዚሁ ወቅት አል ቡርሃን የቱርክን አሸማጋይነት መቀበላቸውን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ባለፈው ወር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ቱርክ ባቀኑበት ወቅት፣ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶዋን አገራቸው ኢትዮጵያ እና ሱዳን የገቡበትን ውዝግብ የማሸማገል ፍላጎት እንዳላት መግለጻቸው መነገሩ አይዘነጋም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img