Monday, October 7, 2024
spot_img

በመንግስት ሸኔ የሚባለው ቡድን በሆሮ ጉድሩ ዞን በጸጥታ ኃይሎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ መስከረም 8፣ 2014 ― በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ሆሮ ጉድሩ ዞን በሽብርተኝነት የተፈረጀው ኦነግ ሸኔ በጸጥታ ኃይሎች ላይ በከፈተው ተኩስ ጉዳት ማድረሱን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አስታውቋል።

የኦሮሚያ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ጌታቸው ባልቻ ጥቃቱ ባለፈው ሳምንት የተለያዩ አካባቢዎች ላይ መድረሱን ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በደረሰባቸው አካባቢዎች ጥቃት እየፈጸመ መሆኑ የተነገረለት በመንግስት “ሸኔ” የሚባለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ሲል የሚጠራው ቡድን ማክሰኞ እና ረቡዕ መስከረም 4 እና 5 በሆሮ ጉድሩ ዞን አንዲት መንደር ውስጥ ተንቀሳቅሶ በሚሊሻና በፖሊስ አባላት ላይ ተኩስ በመክፈት ጥቃት ማድረሱን ጌታቸው ጠቁመዋል። በጸጥታ ኃይሎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከመቁሰል ውጭ የሞተ የጸጥታ አባል አለመኖሩንም ገልጸዋል።

“ሸኔ” ከዚህ በፊት ሲንቀሳቀስባቸው በነበረባቸው አካባቢዎች ላይ ባለፈው ሳምንት ጉዳት ማድረሱን ያስታወሱት ጌታቸው፣ አሁን ላይ ምዕራብ ወለጋም ሆነ ምስራቅ ወለጋ ሠላም እንደሆነና ጥቃት ተፈጸመ ተብሎ መረጃ እንዳልደረሳቸው ተናግረዋል። ነገር ግን በተባለው ልክ ገፍቶ ወጥቶ ጥቃት ባይፈጽምም፣ አሁንም ቡድኑ እንቅስቃሴ እያደረገ በመሆኑ ሥጋቶች መኖራቸውን ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ የክልሉ የፀጥታ ኃይል በተቀናጀ ሁኔታ ክትትል እያደረገ መሆኑን ነው የጠቆሙት።

በሌላ በኩል “ሸኔ” በአሁኑ ወቅት ወታደሮችን በማሠልጠን ላይ ነው ስለመባሉ “ሸኔ” የራሱን ፍላጎት ለማሳካት የማይለው ነገር የለም ያሉት ጌታቸው፣ “ስንት ክፍለ ጦር ወታደር አደራጅተናል፤ ስንት አስታጥቀናል፤ ይህን ወረዳ ይዘናል፤ ይህን ቀበሌ ተቆጣጥረናል የማይልበት ቀን የለም ሁሌ ነው እንዲህ የሚለው። ነገር ግን አንድ ቀበሌ ይቅርና አንድ መንደር እንኳን ይዞ የቆየበት ጊዜ የለም” ሲሉ ገልጸዋል ሲል የዘገበው አዲስ ማለዳ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img