Sunday, September 22, 2024
spot_img

በትግራይ ተፋላሚ ኃይሎች የተኩስ አቁም እንዲያደርጉ የጸጥታው ምክር ቤት እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጳጉሜን 3፣ 2013 ― በትግራይ አስር ወራት በተሻገረው ጦርነት ተፋላሚ ኃይሎች ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እርምጃ እንዲወስድ የጠየቀው ለመላው ዓለም ሰላም፣ ፍትሕ እና ሰብአዊ መብቶች መከበር ይሠራል የሚባለው ግሎባል ሊደርስ የተባለው የዓለም አንጋፋ ፖለቲካ መሪዎች ቡድን ነው፡፡

ይኸው በቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ኔልደን ማንዴላ የተመሠረተው ቡድን ለጸጥታው ምክር ቤት አባላት በኢትዮጵያ የዜጎችን ሰቆቃ ማስቆም የሚቻልበት ብቸኛ አማራጭ የተኩስ አቁም መሆኑን አስረድቷል፡፡

ጥያቄውን በቀድሞዋ የአየርላንድ ፕሬዝዳንትና በሊቀመንበሩ ማሪ ሮቢንሰን ያቀረበው ቡድኑ፣ መሬት ላይ እውነታ ለመገንዘብ እና ይበልጥ ትኩረት እንዲያገኝ የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ወደ ትግራይ ጉዞ እንዲያደርጉ መክሯል፡፡

ለጸጥታው ምክር ቤት በግሎባል ሊደርስ የቀረበውን ጥሪ፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድርጅት የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ሊንዳ ግሪንፊልግ ድጋፍ አግኝቷል፡፡

ግሎባል ሊደርስ ገለልተኛ ድርጅት ሲሆን፣ የቀድሞው ሥመ ጥር የዓለም መሪዎችን ያቀፈ ስብስብ ነው፡፡ ስብስቡን መስራቹን ኔልሰን ማንዴላን ጨምሮ ዴዝሞን ቱቱ እና ኮፊ አናን መርተውታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img