Monday, September 23, 2024
spot_img

በሱዳን ያሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ቢቀንስም ስደተኞቹ የት እንደገቡ ግን እንደማያውቅ የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን ገለጸ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጳጉሜን 3፣ 2013 ― የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) በሱዳን በሚገኙ ካምፖች ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ቢቀንስም፣ እነዚህ ስደተኞች በአሁኑ ወቅት የት እንደሚገኙ ግን እንደማያውቅ ገልጧል፡፡

ድርጅቱ ይህን ያለው መንግሥት በሱዳን ለስደተኞች የሚሰጥ መታወቂያን የያዙ ግለሰቦች ከህወሓት ወገን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው ማለቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ ዩኤንኤችሲአር የሚሰጠውን የስደተኞች መለያ መታወቂያ የያዙ ታጣቂዎች ከሱዳን ድንበር ተሻግረው ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሁም ወደ አማራ ክልል ሰርገዋል ሲል ወንጅሏል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ለዚሁ ምላሽ ባወጣው መግለጫ፤ ከስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚወጡት ስደተኞች የት እንደሚሄዱ የሚያረጋግጥበት መንገድ እንደሌለው አስታውቋል።

ባለፉት ጥቂት ወራት በሱዳን የስደተኞች መጠለያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር በተወሰነ ደረጃ እንደቀነሰ ገልጾ፤ “ዩኤንኤችሲአር ወደ ትውልድ አገራቸው የተመለሱ ስደተኞችን ጨምሮ ከስደተኞች መጠለያ የወጡ ግለሰቦች የት እንዳሉ ማረጋገጥ አይችልም” ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ሱዳን ውስጥ የመዘገባቸው አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው በጦርነት ስለመሳተፋቸው በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን መዘገቡን እንደሚያውቅም ዩኤንኤችሲአር አመልክቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img