አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጳጉሜን 3፣ 2013 ― ትምህርት ሚኒስቴር የአለም አቀፍና የማህበረስብ ትምህርት ቤቶች ፈቃድ አሰጣጥና ዕድሳት መመሪያን መሰረት አድርጎ ስኩል ኦፍ ኔሽን ትምህርት ቤት ላይ እገዳ መጣሉን አስታውቋል፡፡
አዲሱ የትምህርት ዘመን ከመጀመሩ በፊት በትምህርት ክፍያ ጭማሪ ዙሪያ በተደጋጋሚ ከወላጆች ቅሬታ በመቅረቡ የትምህርት ሚኒስቴር የዘርፍ አመራሮችና የባለሙያዎች ቡድን ትምህርት ቤቱንና የወላጅ ኮሚቴውን በማወያየት ከስምምነት ላይ እንዲደርሱ በተደጋጋሚ ጊዜ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል መቆየቱን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ፣ በተደረጉት ውይይቶች ስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻሉ ትምህርት ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ መታገዱን እወቁት ብሏል፡፡
የታገደው ትምህርት ቤት ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ መሰረት ከወላጅ ኮሚቴ ጋር ፈጥኖ በመነጋገር ሪፖርት እስኪያደርግ ድረስ ምንም አይነት የትምህርት ስራ እንዳይሰራ ተብሏል፡፡