Monday, October 7, 2024
spot_img

አደገኛው የኮቪድ ዴልታ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ይፋ አደረገ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጳጉሜን 2፣ 2013 ― አደገኛው የኮቪድ ዴልታ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ይፋ አደድርጓል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሰጡት መግለጫ “በኢትዮጵያ ባለፉት ሳምንታት በወረርሽኙ የሚያዙ ሰዎች፣ የሚሞቱና ፅኑ ህሙማን ቁጥር በጣም አሻቅቧል” ብለዋል።

አዲሱ ዝርያ ሁሉንም የዕድሜ ክልል የሚያጠቃ፣ ለከባድ ህመምና ሞት የሚዳርግ በተለይም ባልተከተቡ ሰዎች ላይ የሚበረታ ዝርያ መሆኑን ገልፀዋል።

ክትባት በየጤና ተቋማቱ በመገኘት እንዲወስዱ፣ የኮቪድ ፕሮቶኮልን ከሁሉም ተቋማትና ግለሰቦች እንደሚጠበቅም አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት ብቻ 8 ሺህ 300 ሰዎች በወረርሽኙ ሲያዙ እስካሁን በአገሪቱ 313 ሺህ ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል። እስካሁን ድረስም ከ4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሳቢያ ሕይወታቸው አልፏል።

በኮቪድ ወረርሽኝ የመያዝ ምጣኔውም ከ1 በመቶ ወደ 20 በመቶ አሻቅቧል፤ ባለፈው ሳምንት 118 ሰዎች ሞተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img