Monday, October 7, 2024
spot_img

ሕወሓት ለ55 የተለያዩ አገራትና ተቋማት በፌደራል መንግሥት ላይ ጫና እንዲደረግ የሚጠይቅ ደብዳቤ ጻፈ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጳጉሜን 2፣ 2013 ― በሕዝብ ተወካችዮ ምክር ቤት በሽብርተኝነት ቢፈረጅም የትግራይ ክልል ሕጋዊ መንግሥት መሆኑን የሚገልጸው ሕወሓት በአመራሩ በዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የተጻፈ ደብዳቤ ለ55 የተለያዩ አገራትና ተቋማት ደብዳቤ ልኳል፡፡

ሕወሓት በደብዳቤው ደብዳቤው የደረሳቸው አገራትና ተቋማት በፌደራል መንግሥት ላይ ጫና እንዲያደርጉ እንዲሁም የትግራዩን ጦርነት ለመፍታት ሁሉን ዓቀፍ ድርድር እንዲደረግ ጠይቋል፡፡

ችግሩ ለመፍታት የመጀመሪያው ርምጃ በድርድር ላይ የተመሠረተ ተኩስ አቁም እንደሆነ አጽንዖት የሰጠው ደብዳቤው፣ በትግራይ ላይ መንግሥት የጣለው የኮምንኬሽን እገዳ በቶሎ እንዲነሳ፣ ያልተገደበ ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲገባ የኤርትራ ወታደሮችና የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች ክትግራይ እንዲወጡ መጠየቁም ተመላክቷል፡፡

በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የሕወሃት ተዋጊዎች ፈጽመዋል የሚባለውን ወንጀል ያስተባበለው ደብዳቤው፣ የመብት ጥሰት ካለ በገለልተኛ አካል ይጣራ ብሏል፡፡
ሕወሃት ለአገራቱ እና ተቋማት የላከውን ደብዳቤ በተመለከተ ከፌዴራል መንግስት የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡

በሕወሓት እና በፌዴራል መንግስት መካከል የሚደረገው ጦርነት ከጀመረ አስር ወራት ተሻግሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img