Sunday, November 24, 2024
spot_img

የሱዳን የሃገር ግዛት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጭነው ወደ ካርቱም የገቡ ጦር መሳሪያዎች ተያዙ መባሉ ከእውነት የራቀ ነው አለ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጳጉሜን 2፣ 2013 ― በኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጭነው ወደ ካርቱም የገቡ ጦር መሳሪያዎች ተያዙ በሚል የሚናፈሰው ከእውነት የራቀ ነው ሲል የሱዳን የሃገር ግዛት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በካርቱም አየር ማረፊያ የጉምሩክ ኃላፊዎች የተያዘው “ጦር መሳሪያ” ምንም ዐይነት የሕግ ግድፈት እንደሌለበት ነው የገለጸው፡፡

የጦር መሳሪያዎችን እንዲያስመጣ ህጋዊ ፈቃድ ባለው ‘ዋዒል ሸምሰዲን’ የተባለ የንግድ ተቋም ተገቢውን የጉምሩክ ህግ ጠብቀው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ወደ ካርቱም መግባታቸውንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

ንብረቶቹን ለባለቤቱ ለማስረከብ ተገቢው የጉምሩክ ክሊራንስ ሂደት ተጀምሯልም ብሏል፡፡

የጉምሩክ ኃላፊዎቹ ተገቢው ፈቃድ ሳይሰጥ ከኢትዮጵያ የመጡ ናቸው በሚል የያዟቸው 290 የአደን ጥይቶችን የያዙ 73 ካርቱኖች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በተስማማው መሰረት ህጋዊ ሂደታቸውን ጠብቀው ወደ ካርቱም መግባታቸውንም የንብረቱ ባለቤት ‘ዋዒል ሸምሰዲን’ አስታውቋል፡፡

‘ዋዒል ሸምሰዲን’ ለሲቪል ግልጋሎት የሚውሉ ጦር መሳሪያዎችን ከውጭ የማስገባት እና የመነገድ ፈቃድ ያለው ድርጅት ነው፡፡

እንደ ድርጅቱ ጠበቃ ሲራጁዲን ገለጻ ከሆነ የሩሲያው ጦር መሳሪያዎች አምራች ‘ክላሽንኮቭ ኮንሰርን’ የሱዳን ወኪል ሆኖም ይሰራል፡፡

በትላናትናው እለት በሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና) የቀረበብን ዘገባ የተዛባ እና ከእውነት የራቀ ነው ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ መሳሪያዎቹ በተገቢ የስምምነት ሰነዶች በአደራ የተረከብኳቸው ናቸው ብሎ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img