Monday, October 7, 2024
spot_img

የአዋሽ ወንዝ ሙላት ከ1 ሺህ 400 በላይ አባወራዎችን አፈናቀለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጳጉሜን 1፣ 2013 ― በየዓመቱ ከላይኛው የተፋሰሱ አካባቢዎች እስከ ታችኛው የአፋር ምድር ከባድ ጎርፍ በማስከተል ነዋሪዎችን የሚያፈናቅለው የአዋሽ ወንዝ ሙላት ዘንድሮም በላይኛው የወንዙ ተፋሰስ ከ1 ሺህ 400 በላይ አባወራዎችን አፈናቅሏል፡፡

በወንዙ ሙላት ጉዳት የደረሰባቸው በሶስት ዞኖች ውስጥ የሚገኙ አራት ወረዳዎች ነዋሪዎች በአዋሽ ወንዝ ጎርፍ ምክንያት ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል አሊያም ወንዙ ዙሪያ ገባውን ከቦ በስጋት እንደሚኖሩም ነው የተገለጸው፡፡

ዶይቼ ቨለ ነዋሪዎች ነዋሪዎች ነግረውኛል ብሎ እንደዘገበው ክረምት በመጣ ቁጥር ስጋትን የሚደቅነው የአዋሽ ወንዝ፣ ዘንድሮም ወንዙ የማፋሰሻ ቦዩን ሰብሮ በወጣባቸው አከባቢዎች ባስከተለው የውሃ መጥለቅለቅ ነዋሪዎችን ከቀያቸው አፈናቅሏል አልያም በእርሻ ማሳቸው ላይ የተዘራውን ሰብል ላይመለስ አውድሟል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img