Monday, October 7, 2024
spot_img

መንግሥት በዋሺንግተን ሥመ ጥር አዲስ የሎቢ አድራጊ ድርጅት ቀጠረ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጳጉሜን 1፣ 2013 ― የኢትዮጵያ መንግስት በዋሺንግተን ሥመ ጥር እንደሆነ የተነገረለት ሜርኩሪ ፐብሊክ አፌይርስ የተባለ አዲስ ሎቢ አድራጊ መቅጠሩ ታውቋል፡፡

አምባ ዲጂታል ያገኘው ሰነድ እንደሚያመለክተው ሜርኩሪ ከተባለው መሠረቱን እንግሊዝ ካደረገ የሎቢ አድራጊ ተቋም ጋር ውል የተፈራረሙት በአሜሪካ የሚትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ናቸው።

ይህንኑ የሎቢ አድራጊውን ቅጥር አምባሳደር ፍጹም አረጋ ያረጋገጡ ሲሆን፣ የሎቢ አድራጊው ቅጥር በአገር ቤት እና በውጭ አገራት ላሉ ዜጎች ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተደረገ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት የሚያደርገው ጫና በርትቷል በሚባልበት ወቅት በመንግስት የተቀጠረው ሜርኩሪ ፐብሊክ አፌይርስ፣ ወቅታዊውን የኢትዮጵያ ጉዳይ በተመለከተ ከሚዲያዎች እና ከአሜሪካ መንግስት ሹማምንት ጋር ባለው ግንኙነት ላይ የማማከር አገልግሎት እንደሚሰጥ ተነግሮለታል፡፡

አሁን በኢትዮጵያ መንግስት የተቀጠረው ሜርኩሪ፣ ከአገራት ለሌላኛዋ የምሥራቅ አፍሪካ አገር ኡጋንዳ እንዲሁም ለሞዛምቢክ እንደሚሠራ የተገለጸ ሲሆን፣ የሊቢያን የባለ አደራ ጊዜ መንግስትም ያማክራል ነው የተባለው፡፡

ከአገራት በተጨማሪም በአሜሪካ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ግሩፕ ተቀጥሮ መስራቱም የተነገረ ሲሆን፣ በቅርቡ ደግሞ በዚያው በአገሪቱ ለሚገኘውና ለኢትዮጵያ መንግስት ቅርበት አለው ለሚባለው ለሌላኛው የዲያስፖራ ግሩፕ ኢትዮጵያን ፐብሊክ አፌርስ ኮሚቲ የተቀጠረ ነው፡፡

አዲሱን የመንግስት ሎቢ አድራጊ ቅጥር በተመለከተ ለሕወሃት በሎቢ አድራጊነት የሚሠራው ቮን ባተን ሞንቲግዩ፣ መንግስት ስመ ጥር የሎቢ አድራጊ ቢቀጥርም እየሠራበት የሚገኘው ኢትዮጵያ በአሜሪካ መንግሥት ከ20 ዓመታት በፊት የተሰጣትን ከታሪፍና ከኮታ ነፃ የሚያደርገውን ‹‹አፍሪካን ግሮውዝ ኤንድ ኦፖርቹኒቲ አክት›› (አጎዋ) ተጠቃሚነት የማጣቷ ጉዳይ ግን ያበቃለት ነው ሲል ቅጥሩ የሚያመጣው ለውጥ እንደሌለ አሳውቋል፡፡

መንግሥት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ቬኔብል የተሰኘ በአሜሪካ የኮንግረስ አባላትን ለመጎትጎት የሚሠራ የጥብቅና ድርጅት በ35 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወርሃዊ ክፍያ መቅጠሩን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img