Friday, October 18, 2024
spot_img

የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር መንግስት እና ሕወሓትን ለማደራደር ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 29፣ 2013 ― የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር መንግስት እና ሕወሃትን ለማደራደር ጥያቄ ማቅረባቸውን የደቡብ ሱዳን መንግስት ባለሥልጣንን ጠቅሶ አናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

የአገሩ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ሚካኤል ማኩዌ የአገራቸው ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ዐብደላ ሀምዶክ ጥያቄ ይህንኑ ይዘው ወደ ኢትዮጵያ አምርተው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቅርበው የእሺታ መልስ ማግኘታቸውን፣ እንዲሁም ጠ/ሚ ዐቢይ ኪር ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ውዝግብ እንዲያሸማግሉ መጠየቃቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡

ሳልቫ ኪር ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ በኢጋድ ሊቀመንበሩ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሀምዶክ ‹‹ለማደራደር ትክክለኛው ሰው›› ታምኖበት መሆኑን ዘገባው አክሏል፡፡

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ነሐሴ 20 ወደ ኢትዮጵያ መጥተው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል እንደተደረገላቸው ይታወሳል፡፡

ሆኖም ይኸው የደቡብ ሱዳን መንግስትንና ሕወሃትን የማሸማገል ጥያቄ ጉዳይ በፌዴራል መንግስትም ሆነ በሕወሓት በኩል ምላሽ አልተሰጠበትም፡፡

ከመንግስት እና ከሕወሃት ሽምግልና ጋር በተገናኘ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ አሁን ለሳልቫ ኪር ወደ ኢትዮጵያ ሄደህ መንግስትን አነጋግር የሚል ትእዛዝ ሰጥተዋል የተባሉት የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብደላ ሀምዶክ የማደራደር እቅድ እንዳላቸው ቢነገርም፣ በኢትዮጵያ በኩል ሱዳን ለማደራደር ወሳኝ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን ተዓማኒነት አታሟላም የሚል መልስ መሰጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img