Monday, October 14, 2024
spot_img

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ስራውን ለመጀመር የሚያስችሉ ዝግጅቶች መጀመሩን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 29፣ 2013 ― ሳፋሪኮም ቴሌኮምዩኒኬሽንስ በኢትዮጵያ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

የድርጅቱ ኃላፊዎች ለመገናኛ ብዙሃን ገለጻ ባደረጉበት ወቅት ሳፋሪኮም ቴሌኮምዩኒኬሽንስ የኢትዮጵያ ቢሮውን የሚመሩ የስራ ኃላፊዎችን የመመደብ፤ የሰራተኛ ቅጥርና ቁሳቁስ የማሟላት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በዚህም መሰረት 1000 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የዘርፉ ባለሙያዎችን የመቅጠር ሂደት እንደተጀመረ ተገልጿል፡፡

በተለይም ኩባንያው የኢትዮጵያ ዜጋ የሆኑ ባለሞያዎችን በቴክኖሎጂ፣ ንግድ እና ሌሎች የኮርፖሬሽን ዘርፎች ላይ ከአዲስ ምሩቃን እስከ ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ የስራ እርከኖች ላይ መቅጠር እንደጀመረ ተናግረዋል።

እየተካሄደ ካለው የስራ ቅጥር ሂደትም ቅጥራቸው የተረጋገጠ 11 የኤግዚክዩቲቭ ኮሚቴ አባላቱን በይፋ አሳውቋል።

የሳፋሪኮም ፐብሊክ ሊሚትድ ካምፓኒ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፒተር ንዴግዋ ባለ አክስዮኖቹ ኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለነዋያቸውን ለማፍሰስ እንዲሁም የዲጂታል ኢትዮጵያ ዓላማዎች እውን ለማድረግ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የዲጂታል ኢትዮጵያን ዓላማዎች ማሳካት በሚያስችል መልኩ በ10 ዓመታት ውስጥ 8.5 ቢልየን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስት እንደሚያደርግ ኃላፊዎቹ አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ሁለተኛው የቴሌኮም አቅራቢ የሚሆነው ሳፋሪኮም ሥራውን በቀጣይ ዓመት አጋማሽ እንደሚጀምር ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img