Sunday, September 22, 2024
spot_img

መከላከያ ከሱዳን በመግባት የሕዳሴን ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ሞክሯል ያለውን ኃይል መደምሰሱን አሳወቀ

– ሱዳን በበኩሏ ቡድኑን አስመልክቶ በሚነገረው ጉዳይ እጄ የለበትም ብላለች

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 29፣ 2013 ― የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከሱዳን በመግባት የሕዳሴን ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ሞክሯል ያለውን ቅጥረኛ ሲል የጠራውን ኃይል መደምሰሱን አሳውቋል፡፡

እንደ ሠረራዊቱ መግለጫ ኃይሉ የሕዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረ የሕወሃት ‹‹ቅጥረኛ ሃይል›› ነው፡፡

የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ኃይል ኮማንድ ፖስት የኦፕሬሽን ዘርፍ አሰተባባሪ ኮ/ል ሰይፈ ኢንጊ ‹‹ቅጥረኛ›› ያሉት ኃይል ‹‹የተለያዩ ፀረ ሰው እና ፀረ ተሽከርካሪ ፈንጂዎችን ለማጥመድ የሞከረ ቢሆንም መቋቋም ተስኖት ተበታትኗል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ 50 የቡድኑን አባላት መደምሰሱንና ከ70 በላይ የሚሆኑትን ማቁሰሉን ጠቅሷል፡፡

ከሱዳን በኩል ገብቷል የተባለውን ኃይል በተመለከተ የአገሪቱ ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር አል ጣሒር አል ሐጃ እኛ የደገፍነው ኃይል የለም በማለት ጉዳዩን ማስተባበላቸውን ሱዳን ትሪቡን አስነብቧል፡፡

ቃል አቀባዩ አክለውም የአገራቸው ጦር በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች አገራት የውስጥ ጉዳይ እንደማይገባ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን ከሱዳን እና ግብጽ ጋር የሚያነታርከው በዐባ ወንዝ ላይ የሚገነባው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ከአንድ ወር በፊት መከናወኑ ይታወቃል፡፡ ከዚሁ ሙሌት ቀድሞ ግብጽና ሱዳን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ከማከናወኗ በፊት ስምምነት ላይ መደረስ አለበት የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ሰንብተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img