Friday, November 22, 2024
spot_img

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሊያወያይ መሆኑ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ነሐሴ 29፣ 2013 ― የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፓለቲካ ፓርቲዎችን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 29 ሊያወያይ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በውይይቱ እንዲሳተፉ ጥሪ የደረሳቸው በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኩል ነው ተብሏል።

በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል ከጠዋቱ 2 ሰዓት 30 ጀምሮ ይካሄዳል የተባለው ውይይት ላይ ሀገር አቀፍ እና የክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶ/ር ራሄል ባፌ ገልጸዋል። በውይይቱ ላይ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሳተፉም አመልክተዋል።

በዛሬው ስብሰባ ከእያንዳንዱ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ አራት፤ ከክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች ደግሞ ሁለት አመራሮች እንደሚሳተፉ ጥሪው የደረሳቸው ከሶስት ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ሰምቻለሁ ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። የስብሰባው ግብዣ የፖለቲካ ፓርቲዎች መረጃዎችን በሚለዋወጡበት የቴሌግራም ግሩፕ ትላንት ዐርብ ጠዋት እንደደረሳቸውም ጠቁመዋል።

በውይይቱ እንዲሳተፉ የተጋበዙ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር፤ “የስብሰባው አጀንዳ ‘ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ’ ይበል እንጂ የትኛው ሀገራዊ ጉዳይ አንደሆነ አልተገለጸም” ማለታቸውም ተመላክቷል። የስብሰባ አጀንዳ በተመለከተ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ፤ ውይይቱን ያዘጋጀው የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት በመሆኑ ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img