Friday, October 18, 2024
spot_img

በጎንደር ከተማ ጫት ማጓጓዝ፣ ማስቃምና መቃም ተከለከለ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 28፣ 2013 ― የጎንደር ከተማ የፀጥታ ም/ቤት ባስተላለፈው አስቸኳይ ውሳኔ በከተማዋ ጫት ከሌላ አካባቢ ማጓጓዝ፣ መቸርቸር ማከፋፈል፣ ማስቃምና መቃም መከልከሉን አሳውቋል።

ምክር ቤቱ በመንግስት በሽብረተኛነት የተፈረጀው ህወሓት ከሌሎች ፅንፈኛ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር በመሆን በአማራ ክልል ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች ህዝቡ ላይ ሁሉንም አይነት ግፍ እየፈፀመ ነው፤ የበቀል በትሩንም ማሳረፍ ጀምሯል ብሏል።

አክሎም “ወረራውን ሊመክት የሚችል የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆንና ሃገርን ከጥቃትና ከወረራ እንዲሁም ከጥፋት ለመታደግ ከሱስ የፀዳ በስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ አስፈላጊ በመሆኑ ይህን ትውልድ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት መነሻ በማድረግ በከተማው በጫት አቅራቢዎች አጓጓዦች፣ አከፋፋዮች፣ ቸርቻሪዎች አስቃሚዎቾና ተጠቃሚዎች ላይ የክልከላ ውሳኔ ተላልፋል” ሲል አሳውቋል።

በመሆኑም ከነገ ጀምሮ ምክር ቤቱ ክልከላ ባደረገባቸው ተግባራት ላይ ሲሳተፍ የሚገኝ ተሽከርካሪ ግለሰብም ሆነ ድርጅት በህግ የሚጠየቅ መሆኑን በማሳሰብ፤ የተላለፈውን ክልከላ የከተማዎ የፀጥታ ሃይል ተከታትሎ እንዲያስፈፀም መታዘዙን ምክር ቤቱ አስታቋውል።

በሌላ በኩል በጎንደር ከተማ በጫት ንግድ የተሰማሩ የከተማው ህብረተሰብ ክፍሎች ዘርፍ ቀይረው በሌሎች የንግድ የአገልግሎትና ማኒፋክቸሪንግ ዘርፎች ለመሰማራት በተቋቋመው ግብረ ሃይል አማካኝነት አስፈላጊውን ጥረት እና እገዛ ይደረግላቸዋል ሲል ፀጥታ ምክር ቤቱ ገልጿል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img