Sunday, September 22, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ የአጎዋ አባልነት እጣ ፋንታ በቀጣይ ዓመት ታኅሣሥ ወር ይታወቃል

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 28፣ 2013 ― ኢትዮጵያ በአሜሪካ መንግሥት ከ20 ዓመታት በፊት የተሰጣትን ከታሪፍና ከኮታ ነፃ የሚያደርገውን ‹‹አፍሪካን ግሮውዝ ኤንድ ኦፖርቹኒቲ አክት›› (አጎዋ) ተጠቃሚነት ቀጣይ እጣ ፋንታ በታኅሣሥ ወር ይታወቃል ተብሏል፡፡

ከባለፈው ወር ጀምሮ በሕወሃት በሎቢ አድራጊነት የሚሠራው ቮን ባተንግ ሞንግዩ የተባለ ቡድን ኢትዮጵያን የአጎዋ ተጠቃሚነት እድል ለማሰረዝ የአቤቱታ ደብዳቤውን ለአሜሪካ መንግሥትና ለኮንግረስ ማስገባቱ መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡ ይኸው ቡድን ከትላንት በስትያ ነሐሴ 26 የመጨረሻውን መከራከሪያውን ለአገሪቱ ኮንግረስ ማቅረቡንም አሳውቋል፡፡

በአንጻሩ የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት ለማሰረዝ የሚንቀሳቀሰውን ቡድን ሐሳብ ለማክሸፍ ደግሞ ‹‹አሜሪካን ኢትዮጵያን ፐብሊክ አፌይርስ ኮሚቴ›› የተሰኘ ሌላ ቡድን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ኃይል ኢትዮጵያ ከዕቅዱ ተጠቃሚነት እንድትሰረዝ ያቀረበውን ጥያቄ የአሜሪካ መንግሥት ውድቅ እንዲያደርግ ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

የባይደን አስተዳደር በጉዳዩ ላይ የመጨረሻውን ውሳኔ ለማሳለፍ ቀጣዩን የታኅሣሥ ወር እንደሚጠብቅ ነው የታወቀው፡፡

አጎዋ በአሁኑ ጊዜ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ቀጥረው የሚያሠሩ የውጭ አገር ባለሐብቶችና አልሚዎች፣ ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ትልቁ ምክንያታቸው መሆኑን ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

ኢትዮጵያ በ2012 ብቻ በዚህ የነፃ ገበያ ዕድል ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚገመቱ ምርቶች ወደ አሜሪካ መላኳን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img