Sunday, September 22, 2024
spot_img

የመንግሥታቱ ድርጅት በትግራይ የእርዳታ ምግብ ካለቀ 2 ሳምንት ማለፉን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ነሐሴ 28፣ 2013 ― በትግራይ ክልል የነበረው እርዳታ አቅርቦት ከተጠናቀቀ ሁለት ሳምንት እንደሆነ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ ግራንት ሌይቲ አስታውቀዋል፡፡

አስተባባሪው በትላንትናው እለት ባወጡት መግለጫ አስፈላጊ የሆኑ የሰብዓዊ እርዳታዎችን ማቅረብ አለመቻሉ፣ የነዳጅ እና የጥሬ ገንዘብ እጥረት መኖሩ በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በትግራይ ክልል ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን አጋርተዋል፡፡

በትግራይ ክልል 90 በመቶ የሚሆነው ነዋሪ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልገዋል ያሉት አስተባባሪው፣ 400 ሺህ ያህሉ ደግሞ ረሃብ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል።

ግራንት ሌይቲ እንዳሉት በትግራይ ክልል ውስጥ የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለና የደኅንነት ሁኔታው ቢሻሻልም ክልሉ ‹‹ይፋ ባልሆነ የስብዓዊ እርዳታ እቀባ ስር ይገኛል›› ብለዋል።

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ተመጣጣኝ እርዳታ ለማቅረብ በየቀኑ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብዓዊ ቁስ እና ነዳጅ የጫኑ 100 ተሸከርካሪዎች ወደ ክልሉ መግባት እንዳለባቸውም ቢነገርም፣ የመንግሥታቱ ድርጅት ተቋም ግን ከዚህ ውስጥ እስካሁን ወደ ክልሉ መግባት የቻለው ዘጠኝ በመቶ ብቻ የሚሆኑ ተሸርካሪዎች ናቸው ብሏል።

በአሁኑ ወቅት 172 ተሸከርካሪዎች በአፋር ክልል መቀመጫ ሰመራ መቆማቸውን በመግለጽ ከእሁድ ነሐሴ 16 ወዲህ ወደ ትግራይ የገባ የሰብዓዊ እርዳታ የጫነ ተሸከርካሪ አለመኖሩም ተገልጿል።

የመንግስታቱ ድርጅት አስተባባሪ ግራንት ሌይቲ በተመሳሳይ በአማራ እና አፋር ክልል ደግሞ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሕዝብ ለረሃብ ሊጋለጡ ከጫፍ መድረሳቸውን አመልክተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img