Friday, November 22, 2024
spot_img

ዜና እረፍት ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ‹‹ወርቃማው›› እየተባለ ለሚጠራው ዘመን ተጠቃሽ ከሆኑት ድምጻዊያን መካከል የሆነው ዓለማየሁ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል፡፡

በአዲስ አበባ የተወለደው ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ በ79 ዓመት እድሜው ትላንት እኩለ ሌሊት በድንገት ማለፉ ነው የተነገረው፡፡

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በአርበኞች ት/ቤት ተከታትሎ ባደረበት ጥልቅ የሙዚቃ ስሜትና ባለው ግሩም ተሰጥኦ ለመጀመርያ ጊዜ በ1955 በፖሊስ ሠራዊት ሙዚቃ ክፍል ድምጻዊነትን የጀመረው ዓለማየሁ እሸቴ፣ ‹‹ተማር ልጄ››፣ ‹‹አዲስ አበባ ቤቴ››፣ ‹‹ማን ይሆን ትልቅ ሰው››፣ «ማሪኝ ብዬሻለሁ»፣ ‹‹ጥቁር ግስላ›› እና ሌሎችንም በአድማጮች ዘንድ የተወደዱ ሥራዎችን አበርክቷል፡፡

ድምጻዊ ዓለማየሁ እሸቴ በ1957 በትዳር ከተጣመራቸው ወይዘሮ አየሁ ከበደ ጋር ሰባት ልጆችን እንዲሁም የልጅ ልጆችን አፍርቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img