Friday, October 18, 2024
spot_img

በትግራይ ጦርነት ተጨማሪ 11 የረድኤት ሠራተኞች መገደላቸው ይፋ ሆነ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 27፣ 2013 ― በትግራይ ክልል ጦርነቱ ከጀመረ አንስቶ መገደላቸው ይፋ ከተደረጉ 12 የረድኤት ሠራተኞች ተጨማሪ 11 ሌሎች መገደላቸውን ተከትሎ የሟቾቹ ቁጥር 23 መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ተገድለዋል ያላቸው ተጨማሪ 11 የረድኤት ሠራተኞች በክልሉ የሚነቀሳቀሰው የማህበረ ረድኤት ትግራይ ባልደረቦች ናቸው፡፡

የግድያውን ይፋ መደረግ ተከትሎ የተናገሩት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ የሆኑት ግራንት ሊያቲ ግድያው ኮንነዋል፡፡

በትግራይ ክልል በተመሳሳይ ባሳለፍነው ሰኔ ወር የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ባልደረባ የሆኑ ሦስት ሰዎች መገደላቸው መነገሩ ይታወሳል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img