Friday, October 18, 2024
spot_img

በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበል ኤርትራ አስታወቀች

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ነሐሴ 27፣ 2013 ― የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደሚደግፍ እና በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደሚያወግዝ የኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር አስታውቋል፡፡

የግንባሩ ዋና ፀሐፊ አል-አሚን ሙሐመድ አሊ ይህን ያስታወቁት የኤርትራ አብዮትን 60ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው፡፡

በአሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ በምትከተለው የተዛባ ፖሊሲ እና በምታደርገው ጣልቃ ገብነት ምክንያት የቀጣናው ሀገራት በግጭት መታመሳቸውን ቀጥለዋል ብለዋል፡፡

አያይዘውም ሀገራቸው ኤርትራ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እንደምትደግፍ እና በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት እንደማትቀበለው አረጋግጠዋል፡፡

‹‹የአፍሪካ ቀንድን ለመበታተን ይፈልጋሉ›› ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ እንደ ማሳያ በሶማሊያ አድርገውታል ያሉትን እና ዛሬም በኢትዮጵያ እያደረጉት ነው ያሉትን አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ስላለው ነገር በማንሳትም የውስጥ ጉዳይ ስለሆነ አይመለከታቸውም ብለዋል፡፡

የኤርትራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር ዋና ፀሐፊ አል-አሚን ሙሐመድ አሊ አክለውም የአሜሪካ አጀንዳ የአፍሪካ ቀንድን መበታተን ነው፤ የእኛ ምርጫ ደግሞ ከኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ጅቡቲ ጋር በትብብር በመሥራት ሰላምን ማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img